32,99 €
inkl. MwSt.
Versandkostenfrei*
Versandfertig in über 4 Wochen
payback
16 °P sammeln
  • Broschiertes Buch

ምስሌን ፍለጋ የተሰኘው ልብወለድ+ከፊል ግለ ታሪክ+የስብዕና እድገትን በአንድ የያዘው የተለያየ የድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎች በተለይ ወጣቶች ቢያነቡ ብዙ የሚያተርፉበት መፅሀፍ ነው። መጽሐፉን አንጋፋ የስነ-ጽሑፍ ባለሞያዎች በአርትኦት እንዲሁም በመገምገም እና አስተያየት በመስጠት ተሳትፈውበታል። ደራሲዋ ስለመጽሐፉ እንደዚህ ትላለች .... "በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እኔን(ሐና ኃይሉን) በትናንት ትዝታዬ እና በነገ ምናቤ መሀል አስቀምጬ በፈጠርኳቸው የልቦለድ ታሪኮች ውስጥ ታገኙኛላችሁ። ይህ መጽሐፍ ትናንትናዬን የታዘብኩበት ነገዬን ደግሞ በምናቤ ያስተዋልኩበት ሁነኛ ሰነዴ ነው ብዬ አምናለሁ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በምናብ የተፈጠሩ አስደናቂ ሰዎች ያሉትን ያህል፣ በትናንት ትዝታዬ ውስጥ በሕይወቴ የነበሩ፣ አሁንም ያሉ ሰዎች ይገኙበታል። ይህን መጽሐፍ "ምስሌን ፍለጋ" ብዬ እንድሰይመው ያደረገኝ ዋነኛ ምክንያት፣ እንደሚታወቀው ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ፈጣሪ የሰውን ልጅ በአምሳሉ እንደፈጠረው ተገልጿል። መጀመሪያ የተፈጠርንበት ምስል ማለት፣ ከፈጣሪ…mehr

Produktbeschreibung
ምስሌን ፍለጋ የተሰኘው ልብወለድ+ከፊል ግለ ታሪክ+የስብዕና እድገትን በአንድ የያዘው የተለያየ የድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎች በተለይ ወጣቶች ቢያነቡ ብዙ የሚያተርፉበት መፅሀፍ ነው። መጽሐፉን አንጋፋ የስነ-ጽሑፍ ባለሞያዎች በአርትኦት እንዲሁም በመገምገም እና አስተያየት በመስጠት ተሳትፈውበታል። ደራሲዋ ስለመጽሐፉ እንደዚህ ትላለች .... "በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እኔን(ሐና ኃይሉን) በትናንት ትዝታዬ እና በነገ ምናቤ መሀል አስቀምጬ በፈጠርኳቸው የልቦለድ ታሪኮች ውስጥ ታገኙኛላችሁ። ይህ መጽሐፍ ትናንትናዬን የታዘብኩበት ነገዬን ደግሞ በምናቤ ያስተዋልኩበት ሁነኛ ሰነዴ ነው ብዬ አምናለሁ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በምናብ የተፈጠሩ አስደናቂ ሰዎች ያሉትን ያህል፣ በትናንት ትዝታዬ ውስጥ በሕይወቴ የነበሩ፣ አሁንም ያሉ ሰዎች ይገኙበታል። ይህን መጽሐፍ "ምስሌን ፍለጋ" ብዬ እንድሰይመው ያደረገኝ ዋነኛ ምክንያት፣ እንደሚታወቀው ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ፈጣሪ የሰውን ልጅ በአምሳሉ እንደፈጠረው ተገልጿል። መጀመሪያ የተፈጠርንበት ምስል ማለት፣ ከፈጣሪ የተሰጠን ሙሉ ዐቅም፣ ንጽሕና፣ ጥበብ እና ዕውቀት የመሳሰሉት በሙሉ ሆነ በከፊል የማንነታችን መገለጫዎች ናቸው። ሥዕሉን አይታችሁ ሠዓሊውን ታደንቃላችሁ" እንደሚባለው ይህንን ከፈጣሪ የተሰጠንን ሙሉ ማንነታችንን ወይም ምስላችንን፣ በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤት፣ በአካባቢ፣ በማህበረሰብ ብሎም በኅብረተሰብ በሚደርሱብን የተለያዩ ተጽዕኖዎች ቀስ በቀስ እየጎደሉ በመሄዳቸው፣ የተፈጠርንበትን መነሻ ምስላችንን እናጣለን።ታዲያ ዛሬ እኛን ያዩ የተመለከቱ ፈጣሪያችንን ያመሰግኑበት እና ያደንቁበት ይሆን? ይህንን ሙሉ ማንነታችንን ለመመለስ ዕለት በዕለት ተጽዕኖዎቹ ያሳደሩብንን አቧራ እያራገፍን፣ የተፈጠርንበትን ምስል መፈለግ ይገባናል። ለዚህም ነው እኔም በሕይወት ጉዞዬ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ በደረሰብኝ ተጽዕኖ የተነሳ ፣ ከፈጣሪ የተሰጠኝን ሙሉ ማንነቴን በማጣቴ የተፈጠርኩበትን ሙሉ ዐቅም፣ ንጽሕና፣ ጥበብ፣ ዕውቀት እና የመሳሰሉትን ፍለጋ በብዙ ከፍታ እና ዝቅታ ውስጥ ያሳለፍሁትን እውነተኛ የሕይወት ታሪኬን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እንደ አንድ የመጽሐፉ ገጸ ባሕሪ አስገብቼ ለአንባቢያን ያቀረብኩት። '' መልካም ንባብ
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.