አንድ ሰው ነበረ፤ የተለየ ልብ ያለው። አኧምሮውን ማዘዝ እና ማስቆም የሚችል ልብ። አኧምሮው ሲያስቆመው አካሉም እዛው ተገተረ። ያለ ተስፋ፣ ያለረዳት፣ እዛው እንድቆመ ፤ ለምን እንደሆነ ባላወቀው ምክንያት፣ ሁሉም ነገር በዙሪያው በፍጥነት ይለዋወጥ ነበር። ለተመለከተው ፊቱ ይናገራል፣ እሱ ለውጡ አልገባውም። እዛው በመንገዱ ዳር እንደቆመ መልኩ ጠፉ፣ ውበቱ ረገፈ። ዓመታት አለፉ። መንገደኛው ሁሉ ይህ ሰው ብቸኛ ነው ብሎ ያዝናል። እሱ ግን ለምን እንደታዘነለት፣ ነገሮችም ሁሉ እየተለወጡ መሆናቸውን አያውቅም። በዚያች ቦታ ለዓመታት ከመቆሙ የተንሳ፣ እርሱ የቦታው ምልክት ሆኗል። ሰው ሁሉ ቦታውን ለመለየት የተለየ ሥዕሎች እና ማስታወቂያ አላስፈልገውም። ሰዎች እሱን እዚያ ቦታ ላይ ለሲሶ ምዕተ ዓመት ያህል ዘመን የገተረው ጉዳይ ምን እንደሆነ አያውቁትም፣ ቢያውቁትም አይገባቸውም። ምክንያቱም ሰዎች ሁሉ እሱ ያለው ዓይነት ልብ የላቸውም ! ይህ መፅሐፍ ግን ስለእርሱ ሳይሆን፤ እርሱ ስለሚያውቃት፣ እና መኖርም መሞትም አቅቷት ስለምትሰቃይ ሴት እንጂ።
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.