መጽሓፉ ሦስት መዕራፎች አሉት። በመጀመሪያው ምዕራፍ ስለ ቁጥሮች እና መሰረታዊ ስሌቶች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ የሥነ-ንጽጽር ቅቡሎች እና ይሁንታዎች በቁንጽል ቀርበዋል። በሦስተኛው ምዕራፍ ዩክሊዳዊ ሥነ-ሥፍራ መሰረታዊ ብይኖች ፣ ይሁንታዎች ፣ አዋጆችን ከነ ማረጋገጫቸው ቀርበዋል። ዘዌዎች ፣ ተማሳይነት ፣ የፓይታጎረስ አዋጅ ፣ ክፍላተ ቅንብባት ከብዙ አዋጆች እና ማረጋገጫ ጋር ተመርጠው ቀርበዋል። የሥነ-ሥፍራ ድርሰቱ የተመረጠው ከቀደምት የግሪክ የሥነ-ሥፍራ ሊቃውንት ድርሰቶች በመሆኑ በዘመናዊ (ትንተናዊ ፣ ካርተሳዊ) ሥነ-ሥፍራ የተቃኘ አንባቢ ከመሰረታዊ ድንጋጌዎች ጀምሮ እያንዳንዱን አዋጅ በርጋታ ማየት ይኖርበታል።
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.