ኢትዮጵያውያን በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለ ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ጭፍጨፋ ሆነ የዐቢይ አህመድ ዓሊና የኢሳይያስ አፈወርቂ ትግራይና የትግራይን ህዝብ ፈጽሞ የማብረስና የማውደውም ዘመቻ እንዳያይና የተቃውሞ ድምጹን እንዳያሰማ ያደረገው የኢትዮጵያ ህዝብ በትግራይ መሬትና በተጋሩ ላይ ምን እየተደረገ እንዳለ ስለማይውቅ ሳይሆን በዋናነት ኢትዮጵያውያን በትግራይ ህዝብ ላይ ያላቸው ስር የሰደደ የመረረ ጥላቻና የምቀኝነት ውጤት ነው። ኢሳይያስ አፈወርቂ፥ ድስትና ማንኪያ፣ አህያና እንቁላል፣ አሸዋና በርበሬ፣ ሊጥና ወጥ እየገለበጠ የሚሰርቅ፣ የሚያጓግዝ፣ የሚዘርፍና የሚመነትፍ ሌብነት የማይገልጸው አሳፋሪ ድርጊት ሲፈጽም፤ ቀሚስ የለበሰች ሁሉ የሚያስነውር ህሊና ቢስ ሠራዊት አሰማርቶ ትግራይን ሲያበርስና ሲያወድም የትግራይ ህዝብ ሲጨፈጭፍና ሲገድል ኢትዮጵያውያን ሳያዩና ሳይሰሙ ቀርተው ሳይሆን ኢሳይያስ አፈወርቂና ሠራዊቱ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ሲሉ በደስታ ስለ ተቀበሉት ብቻ ነው። በትግራይ ህዝብ ላይ የተገለጠው ኢትዮጵያዊነት ዓለማችን ያላያቸውና ያልሰማቸው የጭካኔ ዓይነት እውን የሆነበት ክስተት ከመሆኑ በላይ በትግራይ እናቶችና ሴቴቶች፣ ግራና ቀኛቸው በማያውቁ ህጻናትና በደከሙ ሽማግሌዎች ላይ የተፈጸመው ግፍና በደል እያየና እየሰማ "በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ" የሚል ዜጋ ቢኖር ሰውና ፈጣሪ የማይፈራ፣ የንጹሐን ዜጎች ደም መጋት የለመደ፣ ፍርድን ወደ ሐሞት የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት እየለወጠ በከንቱ ነገር ደስ የሚለው፣ አእምሮው ያጣ የበከተ ዜጋ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። አንድም፥ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በካህን እጅ የውኃ ጥምቀት የተጠመቀ፣ እግዚአብሔር አምላክ በእውነትና በጽድቅ የሚያመልክ፣ ለደንቆሮው እግዚአብሔር ይሰማለታል ለዕውሩም እግዚአብሔር ያይለታል ብሎ የሚያምን ንጹህ ህሊና ያለው ሰው የስምንት ዓመት ህጻን ልጅና የሰማኒያ ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ እናት ክብረ ንጽህና እንደ ውሻ በማስነወርና በማራከስ ደስ አይሰኝምና።
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.