መቼም ከሀገር ቤት ወጥቶ ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ ማሰብ ድፍረትን ይጠይቃል ፤ ሁሉን ነገር አውጥቶና አውርዶ ማቀድ ደግሞ ፣ ይበልጥ ጉብዝናን ይጠይቃል ፤ ጓዝን ጠቅልሎ ለመውጣት ግን ፣ ጉብዝናንም ድፍረትንም ይጠይቃል ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞና ተደራርቦ የሚመጣው ጭንቀት ፣ የባህል ግርታ/ ድንጋጤ/ ፣ ግራ መጋባቱ ፣ ከባዶ (ከምንም ) መነሳቱ፣ አንዳንድ ጊዜ የአእምሮ ጤንነታችንን እንኳ እንድንጠራጠር ያደርገናል ፤ ሁላችንም በዚህ ውስጥ እናልፋለንና፡፡ነገሮቹ ግን የተለመዱ ሆነው እናገኛቸዋለን ፡፡ "የስደትን ኑሮ እንዴት እናሸንፍ፡7 የክህሎት ማዕቀፎች "--የሚለው መጽሀፍ ሊዳስስ የሚሞክረው ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ በተለይም ደግሞ በመልማት ላይ ካሉ ሀገሮች ወደ አሜሪካ ( ወይም ወደ ሌላ ሀገር ) ስትሄዱና ፣ ከዚያም በኋላ ባሉት አመታት ልትጋፈጧቸው የምትችሏቸውን ጥቂት ተግዳሮቶች ፣ እንዴት ለይታችሁ ማወቅ እንደምትችሉለማመላከት ነው፡፡ ስለዚህም የራሴና የብዙ ሰዎች በጥበብ የካበተ ታሪክና ልምድ ፣ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ተካተው ቀርበዋል ፡፡ በተጨማሪ ከዚህ መፅሀፍ የምታገኟቸው ትሩፋቶች ፡- * በምታልፉበት ሂደት ውስጥ ብቻችሁን አለመሆናችሁን ፣ * በባህል ውህደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ከበድ ያሉ ተግዳሮቶችንና የአእምሮ ጤና እክልን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ለመወጣት የሚረዱ መሳሪያዎችን ፣ * በከባድ ፈተና ወቅት ፣ ተግዳሮቶችን ማለፍ የሚያስችሉ መሳሪያዎችን መለየት ፣ ፈጠራን መጠቀም እና በአዎንታዊነት የሚረዱ ማለፊያ መንገዶችን ፣ * ባዕድነት (እንግዳነት) እንዳይሰማችሁ ፣ ይልቁኑ አዲሱን መኖሪያችሁን እንድትላመዱ፣ የባለቤትነት (የቤተኝነት) ስሜት እንዲያድርባችሁ ማድረግ እና እትብታችሁ የተቀበ- ረባትን ሀገር ሳትዘነጉ አሜሪካንን መውደድ እንደምትችሉ ፣ * የራሳችሁንም ሆነ የሌሎችን ህይወት እንዴት ማብቃት እንደምትችሉ ፣ * የተወለዳችሁበትን ሀገራዊውንና ፣ የመጣችሁበትን አሜሪካዊውን እውቀት የምታዛም ዱበትና አገናኝ ድልድይ የምትዘረጉበት ፣ * የባህል ውህደትን ምንነት መማር ፣ ትክክለኛውን አመለካከት ማዳበር ፣ በውህደት ጉዞ ውስጥ አሸናፊ ሆናችሁ የምትወጡባቸውን እርከኖች ማወቅ ፣ በአዲሲቷ ሀገራችሁ በአሜሪካ ልቃችሁ የምትወጡበትንዕውቀት ማፍራት፣
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.
Hinweis: Dieser Artikel kann nur an eine deutsche Lieferadresse ausgeliefert werden.