7,99 €
7,99 €
inkl. MwSt.
Sofort per Download lieferbar
payback
0 °P sammeln
7,99 €
7,99 €
inkl. MwSt.
Sofort per Download lieferbar

Alle Infos zum eBook verschenken
payback
0 °P sammeln
Als Download kaufen
7,99 €
inkl. MwSt.
Sofort per Download lieferbar
payback
0 °P sammeln
Jetzt verschenken
7,99 €
inkl. MwSt.
Sofort per Download lieferbar

Alle Infos zum eBook verschenken
payback
0 °P sammeln
  • Format: ePub

በዚህ ምድር ላይ እንደ ሰው ልጅ ሲፈጠር ጀምሮ የተለየ ሀይል የታደለ ምንም አይነት ፍጡር የለም፡፡ ሆኖም ይሄንን ሀይል በአግባቡ የመጠቀም ግዴታም ግን አብሮ ተጥሎበታል፡፡ የተሰጠውን ሀይል በአግባቡ ለተፈጠረለት ዓላማ ሲያውለው የሚያገኘው ሽልማት እንዳለ ሁሉ ያንን ሀይል ያለአግባብ ሲጠቀም ደግሞ የሚቀጣው ቅጣት አለ፡፡ የሰው ልጅ ለዓላማ ስለተፈጠረ ያለ ዓላማ እንዲኖር አልተፈቀደለትም፡፡ ይህንን ስል ማን ይከለክለናል? ልንል እንችላለን፡፡ ሆኖም የሚከለክለንም ይሁን የሚቀጣን እራሳችን የተሰጠን ሀይልና፤ ያላከበርነው ህግ ነው፡፡ ያለ ዓላማ ለመኖር መሞከር ማለት ኤሌክትሪክን በዘፈቀደ ከመጠቀም ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ አጠቃቀም እውቀት ሳይኖረን በዘፈቀደ ብንጠቀመው ለአደጋ መዳረጋችን አይቀርም፡፡ ህይወታችንንም ልናጣ እንችላለን፡፡ ይሁንና ለጉዳት የዳረገን መብራት ሀይል ድርጅት ነው ልንል አንችልም፡፡ ምክንያቱም ለጉዳት የዳረገን ኤሌክትሪኩን ያለእውቀት በዘፈቀደ መጠቀማችን ነው፡፡ ይህንኑ የኤሌክትሪክ ሀይል ህጉን ተከትለን በአግባቡ…mehr

  • Geräte: eReader
  • mit Kopierschutz
  • eBook Hilfe
  • Größe: 0.48MB
  • FamilySharing(5)
Produktbeschreibung
በዚህ ምድር ላይ እንደ ሰው ልጅ ሲፈጠር ጀምሮ የተለየ ሀይል የታደለ ምንም አይነት ፍጡር የለም፡፡ ሆኖም ይሄንን ሀይል በአግባቡ የመጠቀም ግዴታም ግን አብሮ ተጥሎበታል፡፡ የተሰጠውን ሀይል በአግባቡ ለተፈጠረለት ዓላማ ሲያውለው የሚያገኘው ሽልማት እንዳለ ሁሉ ያንን ሀይል ያለአግባብ ሲጠቀም ደግሞ የሚቀጣው ቅጣት አለ፡፡ የሰው ልጅ ለዓላማ ስለተፈጠረ ያለ ዓላማ እንዲኖር አልተፈቀደለትም፡፡ ይህንን ስል ማን ይከለክለናል? ልንል እንችላለን፡፡ ሆኖም የሚከለክለንም ይሁን የሚቀጣን እራሳችን የተሰጠን ሀይልና፤ ያላከበርነው ህግ ነው፡፡ ያለ ዓላማ ለመኖር መሞከር ማለት ኤሌክትሪክን በዘፈቀደ ከመጠቀም ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ አጠቃቀም እውቀት ሳይኖረን በዘፈቀደ ብንጠቀመው ለአደጋ መዳረጋችን አይቀርም፡፡ ህይወታችንንም ልናጣ እንችላለን፡፡ ይሁንና ለጉዳት የዳረገን መብራት ሀይል ድርጅት ነው ልንል አንችልም፡፡ ምክንያቱም ለጉዳት የዳረገን ኤሌክትሪኩን ያለእውቀት በዘፈቀደ መጠቀማችን ነው፡፡ ይህንኑ የኤሌክትሪክ ሀይል ህጉን ተከትለን በአግባቡ ስንጠቀም ግን መብራት ልናገኝ እንችላለን፤ ምግብ እናበስልበለን፤ ብዙ ጥቅም እናገኝበታለን፡፡ እኛ የተሰራንባቸውን ነገሮችም በአጽንኦት ብንመለከታቸው በአግባቡ ለዓላማ ካላዋልናቸው ልክ እንደ ኤሌክትሪኩ መልሰው እኛኑ የማጥፋት ሀይል አላቸው፡፡ ልክ እንደ ሂሳባዊ ስሌት ስኬትም አለማቀፋዊ መርህ እንዳለው ለዓለም ካስተዋወቁትና የብዙሀንን አይን ከገለጡት ፈላስፎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚሰለፈው አንድሪው ካርኒጌ የሰው ልጅ በውልደት ስለተሰጠው ስጦታና እሱን በአግባቡ አለመጠቀም የሚያስከትለውን ቅጣት ሲገልጽ እንዲህ አለ ...የሰው ልጅ ገና ወደ ምድር ሲመጣ ከሚታየው አካላዊ ገጽታው በተጨማሪ የተለያዩ የነርቭ ስርአተ ክፍሎችንና እጅግ በጣም የከበረውን ውድ ስጦታ አዕምሮንና ልብን ይዞ ነው፡፡ ከዚህ የፈጣሪ ስጦታዎቹ ጋር ደግሞ ሁለት የታሸጉ ፖስታዎች አብረው አሉ፡፡ አንደኛው ፖስታ ይህን የፈጣሪውን የከበረ ስጦታ በአግባቡ ለተፈጠረለት ዓላማ ለብዙሀን ጥቅም ሲያውለው የሚያገኘውን ሽልማት ዝርዝር የያዘ ሲሆን፤ ሁለተኛው ፖስታ ደግሞ ይህንን የተሰጠንን የፈጣሪን ስጦታ በቸልታ ወይም ባለማወቅ ሳንጠቀምበት ብንቀር የሚጠብቀንን ቅጣት ዝርዝር የያዘ ነው፡፡ ስጦታችንን በአግባቡ በመጠቀም የምናገኛቸው ሽልማቶች አካላዊና አዕምሯዊ ጤንነት፣ የተሟላ ፍቅር፣ ጸጋና በረከት፣ ቀና አመለካከት፣ ልግስና፣ የአዕምሮ ሰላም ሲሆኑ በተቃራኒው አዕምሮአችንንና ልባችንን በአግባቡ ባለመጠቀም ደግሞ የምንቀጣው ቅጣት ስግብግብነት፣ ዳተኝነት፣ ቅናት፣ መሰሪነት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ ቂም፣ ሽብር፣ በቀል፣ ህመም፣ ጭንቀት፣ ፍርሀት፣ ድባቴ፣ ሰቆቃና ድህነት ናቸው፡፡ ይህንን በቀላሉ ለመረዳት ገበሬ በእርሻ መሬቱ አርሶ የሚፈልገውን ቢዘራ የዘራውን በብዙ እጥፍ የማጨዱን ያህል መሬቱን ዝም ብሎ ቢያስቀምጠው በምትኩ አረም፣ አመኬላና እሾህ ይበቅሉበታል፡፡ አመኬላውና እሾሁ የሚበቅሉት በመሬታችን ላለመዝራታችን እንደቅጣት ነው፡፡ የሰውን ልጅ እውነተኛ አቅም ለመመርመር መሬትን እንደምሳሌ መውሰድ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ሰው ከመሬት እንደመሰራቱ መሬትን በመመልከት ውስጥ እራሳችንን በከፊል ማወቅ ስለምንችል ነው፡፡ መሬትን አንድ ሜትር ቆፍረን የምንፈልገውን ዘር መዝራትና ፍሬ ማፍራት እንችላለን፡፡ 20 ሜትር ወደ ውስጥ ብንቆፍር ደግሞ ውሀ ልናፈልቅ እንችላለን፡፡ ትንሽ ጠለቅ ብለን በመመርመር ነዳጅ ልናፈልቅ እንችላለን፡፡ ምናልባት ሌላ 100 ሜትር ወደ ውስጥ ብንቆፍር ደግሞ የተለየ ጠቃሚ ማእድን ልናገኝ እንችላለን፡፡ እዚህ ጋር ግን አንድ ልንገነዘበው የሚገባው ቁምነገር መሬትን የፈለገ አርቀን ብንቆፍራት የመሬቱን ሙሉ አቅም ልናውቅ አንችልም፡፡ ምክንያቱም በዚህ አለም ላይ አንድም ሰው መሬትን እየቆፈረ በመሬት የታችኛው ገፅ ሾልኮ ወደቀ ሲባል አልሰማንም፡፡ የሰው ልጅ የተሰጠው እውነተኛ አቅምም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህንን አቅማችንን ለከፍታ እንድንጠቀመው ደግሞ ከተፈጥሮ ጋር መተባበር ይጠበቅብናል፡፡ ተፈጥሮ ከሰው ልጅ ጋር ለመተባበር ሁሌም ዝግጁ ነች፡፡ እኛ የጠየቅናትን ነገር ለመስጠት ግን ለሚያስፈልገን ነገር መንስዔ እንድንሆን ትጠብቃለች፡፡ የምናጭደውን ፍሬ ከመስጠቷ በፊት እንድንዘራ ትፈልጋለች፡፡ እኛን ለሀላፊነት ከመሾሟ በፊት ትከሻችን ሀላፊነቱን መሸከም መቻል አለመቻሉን ማረግጋገጥ ትሻለች፡፡ ያለንን ከመባረኳና ከማብዛቷ በፊት የተሰጠንን መስጠታችንን ማረጋገጥ ትፈልጋለች፡፡ ተፈጥሮ በነፃ ለምትሰጠን እያንዳንዱ ነገር በምላሹ እኛም እኩሌታውን የመስጠት ሙሉ አቅም ባይኖረንም ለሰው ልጅ ጠቃሚ ለሆኑ ነገሮች መንስኤ መሆን ግን ሁላችንም የተፈጠርንለት ዓላማ ነው፡፡ ሆኖም የብዙዎቻችን ስህተት የሚመነጨው ለመኖር በጣም የሚያስፈልጉን ነገሮች ሳንዘጋጅባቸው፣ ሳናስብና፣ ሳናቅድ እንዲከናወኑልን ከመጠበቅ ነው፡፡ ከተፈጥሮ መገንዘብ የምንችለው ነገር ለእርሻ በተሰጠን መሬት ላይ ሳይታረስና ሳይዘራ የሚበቅለው የማይፈለግ አረምና እሾህ እንዲሁም አመኬላ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ለኛ ከሚያስፈልጉን ተክሎችም ይሁን አዝርዕቶች ውስጥ የኛን ጥረት ሳይፈልጉ፤ ሳንዘራቸው ወይም ሳንተክላቸው የሚበቅሉት በጣት አይቆጠሩም፡፡ ለዚህ ነው እኛም የምንፈልገውን ነገር ማግኘት ካለብን በዘፈቀደ መኖርን ማቆምና ከተፈጥሮ ጋር መተባበር ያለብን፡፡ ለዚህ ነው በማለም፤ በማሰብና፣ በመመርመር መኖር መጀመር ያለብን፡፡


Dieser Download kann aus rechtlichen Gründen nur mit Rechnungsadresse in A, B, CY, CZ, D, DK, EW, E, FIN, F, GR, H, IRL, I, LT, L, LR, M, NL, PL, P, R, S, SLO, SK ausgeliefert werden.